ኅዳር 4 ፣ 2014

የአረቢካ ሲ ቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ የ86 በመቶ ጭማሪ አሳየ

City: Addis Ababaዜናኢኮኖሚ

የአረቢካ ሲ ቡና ዋጋ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ86 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱ ተገለጸ።

Avatar: Henok Terecha
ሄኖክ ተሬቻ

Henok is a reporter at Addis Zeybe. He is passionate about storytelling and content creation.

የአረቢካ ሲ ቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ የ86 በመቶ ጭማሪ አሳየ

የአረቢካ ሲ ቡና ዋጋ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ86 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱ ተገለጸ። ከአንድ ዓመት በፊት በአሜሪካ የቡና ገበያ የአረቢካ ሲ ቡና ሲሸጥ ከነበረበት 110.7 ፓውንድ በአሁኑ ወቅት ከ206.5 እስከ 210 ፓውንድ ባለው ዋጋ እየተሸጠ እንደሚገኝ አዲስ ዘይቤ ከቡናና ሻይ ባለስልጣን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ከ35 በመቶ በላይ ዓለም አቀፍ የአረቢካ ሲ ቡና ፍላጎት የምታቀርበው ሀገረ ብራዚል፤ በገጠማት የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የአቅርቦት ማነስ ተፈጥሮባታል። ይህም የአረቢካ ሲ ቡና ዋጋ በአለም ገበያ እንዲጨምር ዋነኛው ምክንያት መሆኑን የቡናና ሻይ ባለስልጠጣን የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታጠቅ ግርማ ነግረውናል።

ዓለም አቀፍ ገበያ የሚወሰነው በአቅርቦትና ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ሲሆን የተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ፍላጎትን ለማሟላት የማይችል በመሆኑ የዋጋ ጭማሪው ተከስቷል ብለዋል።

“የቡና ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋው መጨመሩ የቡና ላኪዎች ቡናውን የሚሸጡበት ዋጋ ይጨምራል ማለት ነው በዚህ መሰረት የግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙት ቡና አቅራቢዎች፤ አምራች አርሶ አደሮች ድረስ የሚደርስ ትርፍና ኑሮን የማሻሻል ጥቅም ይኖረዋል” በማለት ይገልጻል። 

በአጠቃላይ የቡና ወጪንግድ ባለፈው ሩብ ዓመት ከታቀደው በላይ አፈጻጸም ተመዝግቧል በዋናነት 6 ሀገራት የወጪ ንግዱ ተደራሽ የሚሆንባቸው ከ30 በላይ የሆኑ ሀገራት አሉ ሳኡዲ አረቢያ፤ አሜሪካ፤ ቤልጂየም፤ ጀርመን፤ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ዋነኛ ተረካቢዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 86,000 ቶን ቡና ወደ ውጭ የላከች ሲሆን፥ 327 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ሻይ እና ቡና ባለስልጣን አስታውቋል።

ሀምሌ በተጠናቀቀው የግብይት አመት ሀገሪቱ 250,000 ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 910 ሚሊየን ዶላር ማግኘቷን የባለስልጣኑ አሃዞች ይጠቁማሉ። የኢትዮጵያ ቡና የወጪ ንግድ በበጀት አመቱ 280,000 ቶን እንደሚደርስ እና 1.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ይገመታል።

በአፍሪካ ትልቋ የቡና አምራች በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ ባለው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የወጪ ንግዱ ክፉኛ ቢጎዳም የቡና አምራቾች ግን ለአለም ሀገራት በላኩት ምርት ከዚህ ቀደም ካገኙት የውጭ ምርት በላይ አዲስ ሪከርድ የሚያስመዘግቡብት ዓመት እንደሚሆንም ይጠብቃሉ።

አስተያየት